Full Text;

Second Message of Ayatollah Khamenei to the Western Youth in Amharic

Second Message of Ayatollah Khamenei to the Western Youth in Amharic

Second Message of Ayatollah Khamenei to the Western Youth in Amharic

የወቅቱ የጋራ ስጋትና ጭንቀታችን አሸባሪነት ነው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ በሆነው

ይድረስ ለምዕራባዊያን ወጣቶች

በፈረንሳይ ላይ የተፈጸመው መራራ አሳዛኝና ጭፍን አሸባሪነት ውስጤን ስለነካው ለእናንተ ለወጣቶች መናገር የሚገባኝን ንግግርና የውይይት ምህዳር መፍጠር የግድ ይላል፡፡ ምንም እንኳን ሀቅ መራራ ብትሆንም በአጭሩ ካልገታነው የጋራ የመግባቢያ መንገድ ካልፈጠርን የደረሰውን ጉዳት ከመባዛት አይገደብም፡፡

በማንኛውም የሰው ልጅ ላይ በየትም ቦታ የሚደርስ ጉዳት ለቀረው የሰው ልጅ ሀዘንና ህመም ምክንያት መሆኑ አይቀሬ ነው ፡፡ በሚወዳቸው ወላጆቹ ፊት ዓይኑ እያየ ህይወቱን ሲያጣ ፣ ሲቀጠፍ፣በደስታ ውስጥ የነበረች እናት ከመቅጽበት ሀዘን ሲውጣት፣ባል የሙት ሚስቱን በድን እየጎተተ ወደ ሌላ ቦታ ለማሸሽ ሲጥር ይህን አሰቃቂ ድርጊት የሚመለከተውም ቢሆን ራሱ ትዕይንቱን አይቶ ሳያበቃ ሊሞት እንደሚችል መመልከቱና መገንዘቡ ሰው ለሆነ ሁሉ አሰቃቂ ሰቆቃ ነው ፡፡ሊቋቋመው የማይችል ምሬትና ሽብር ይንጠዋል፡፡ወኔና ስሜቱ ይቀሰቀሳል፡፡ ሰው መሆኑን ይጠላል፡፡ ይህን መሰል ኢሰብአዊ ድርጊት አተርፍበታለሁ ብሎ ድርጊቱ ለፈጸመው ቡድን ወይም ግለሰብ ሳይቀር ሁኔታው ይረብሸዋል፡፡ይዘገንነዋል፡፡ አሰቃቂ ድርጊቱ በፈረንሳይ ወይም በፍልስጤም ወይም በኢራቅ ወይም በሊባኖስ ወይም በሶሪያ ላይ ይፈጽም እንጂ የድርጊቱ አስከፊነት ሰው ለሆነ ሁሉ አሳዛኝ ነው፡፡

በዓለም ውስጥ ለሚገኘውከ1.5 ቢሊዮን ለሚሆነው ሙስሊም ህዝብ በየቀኑ የሚጨፈጨፉት ፣የሚረግፉት፣የሚቃጠሉትና አጥንትና ስጋቸው የትም ቦታ በሚወድቀው ሙስሊሞች ሰቆቃ ሙስሊሙ አንጀቱ ይቆርጠዋል፣ልቡ ይደማል፣ደም እምባ ያለቅሳል፡፡ ይህን መሰል ሰቆቃ የሚጠላና የሚጠየፍ ወገን በአንጻሩ ለአመጽ መነሳሳቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡የዛሬው ሰቆቃ ለነገው ትውልድ የተሸለ ሁኔታ የሚፈጥር ካልሆነ የጥላቻና የመናቆር ሂደት ቀጣይ ይሆናል፡፡በመሆኑም የተሻለ ህይወት ሊሰፍን የሚችልበትን መንገድ የማመቻቸቱ ሃላፊነት በእናን ወጣቶች ላይ የወደቀ በመሆኑ ይህን አስከፊ ሁኔታ ለመለወጥ የሚያስችል አዲስ ዘዴ መፍጠር ይኖርባችኋል፡፡

ምዓራባዊ ዓለም ከተያያዘው የተንኮል አዙሪት ሊወጣ የሚችልበትን መስመር የመቀየሱ ስራ ለእናንተ ለወጣቶች የተተወ ነው፡፡በአንድ ጫፍ ብቻ ያዘነበለ ሚዛኑን የሳተ የምዕራባዊያን አካሄድን ልትለውጡት መቻል ይኖርባችዋል፡፡

በፈረንሳይ ወይም በፍልስጤም ወይም ደግሞ በኢራቅ እንዲሁም በሊባኖስ እና በሶሪያ የተለኮሰው እሳት ምን ያህል የሰውን ዘር እያጠፋ እንደሆነ ማንም የሚመሰክረው ሀቅ ነው፡፡ይህ አሰቃቂ ትዕይንት ሊቀጥል መቻል የለበትም ፡፡በእርግጥ አሸባሪነት የጋራ ጥላታችን ነው፡፡ለሁላችንም የእለት ተዕለት ጭንቀት ነው፡፡ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአላማችን ጸጥታና ሰላም ያለመስፈን ያሳስበናል፡፡በኢራቅ ህዝብ ላይ በየመን በሶሪያ እና በአፍጋኒስታን በየዕለቱ የሚፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች በሙስሊሙ ዓለም አሰቃቂ ተሞክሮዎች ናቸው፡፡በየጊዜው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት በጭካኔና በግፍ የተጨፈጨፉት ንጹሀን ህዝቦችበቀላል ዘመን ተተርኮ የሚገለጽ አይደሉም፡፡ለዚህ አስከፊ ተግባር መሪተዋናይ በመሆን የጭፍጭፋ ስልትና ዘዴዎችን የሚያቀናጁት የተወሰኑ ሃያላን መንግስታት መሆናቸው ግለጽ ነው፡፡

ዩኤስ አሜሪካ አልቃኢዳን በማሰልጠንና በማስታጠቅ እየፈጠረ ያለውን ትርምስ ብዙ ህዝብ ላያውቅ ይችላል፡፡ታሊባኖችን እስከአፍንጫቸው በማስታተቅ ጠንካራና አስፈሪ ሀይል ሆነው እንዲቀጥሉ እያደረገ ያለው

ዩ- ኤስ አሜሪካ ነው፡፡ከዚህ ቀጥተኛ እርዳታ በስተጀርባ የተክፊሮች እንቅስቃሴ እንዲጎለብት በማድረግ የአሸባሪነት ምህዳር ሰፍቶ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ ተክፊሮች የምዕራባዊያን ጉዳዩ አስፈጻሚ በመሆን በአረጃና በአፈጃ የፖለቲካ ሥርዓት ላይ በመንተራስ በአለም ላይ ጥፋትን እያነገሱ መጥተዋል፡፡የዲሞክራሲን መስመር የሚከተሉና የሰባዓዊ መብትን ለማስጠበቅ የሚጥሩ እውነተኛ ሃይሎች እንዲታፈኑ አድርገዋል፡፡ለምዕራባዊያን ቃልና ተግባር አለመጣጣም ዋናው ማስረጃ ይሄ ነው፡፡በመሆኑም እነደኔ እምነት የወቅቱን ተጨባጭ ሁኔታ በመገንዘብና በመረዳት የአለም ህዝብ ከመከራና ስቃይ የሚላቀቅበትን መንገድ ፈጣሪዎች እናንተ ወጣቶች ናችሁ፡፡ በተለይም ምዕራባዊያን ወጣቶች፡፡

ሌላው የሚጣረስ አካሄዳቸው አሸባሪነትን በመንግስት ደረጃ ድጋፍ በማድረግ እንዲንሰራራ ሲያደርጉት ጭቁን የፍልስጤን ህዝብ በጨካኝ እና ኢ-ሰብአዊ በሆነው የእስራኤል መንግስት አሸባሪነት ያሰቃዩታል፡፡አውሮፓውያን ላለፉት ሰልሳ ዓመታት በሰላም በቤታቸው የኖሩ ሲሆን ፍልስጤናዊያን ግን በቤታቸው የመኖር ነጻነት ተነፍገው በጽዩናዊያን ተንኮል ቤት ንብረታቸው ሲወድም፣ ህይወታቸው ሲጠፋ፣በየቀኑ የሚታዩ ትዕይንት ነው፡፡እስራኤላዊያን በቀየሱት አዲስ የመኖሪያ ሰፈር አልፎ አልፎ የሚታየው ግጭት ወደር ከሌለው የፍልስጤናዊያን ጭፍጨፋ ጋር ማነጻጸር ፍትሀዊነት የጎደለው ነው፡፡ የጺዮናዊያን የሰፈራ መንደር ትንሽ በተነካ ቁጥር ዓለም አቀፍ ድርጅት ነን ባዮች የሚያሰሙት ጩከት ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን የፍልስጤናውያን መኖሪያ ቤቶች በዶዘር ሲደመሰሱ ድርጅታቸው ሲፈራርሱ አትክልቶቻቸው ሲነቃቀሉና ሲወድሙ ገለልተኛ ወገን ነን የሚሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለዓለም ህብረተሰብ ምንም ዐይነት የሚያሰሙት ድምጽ የለም ይህነው እንግዲህ የምዕራባዊያን ዲሞክራሲያዊነት፡፡

ፍልስጤማዊያን እናቶች ቤታቸው ፈርሶ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው ደም እንባ እያለቀሱ ንብረታቸውን ለመሰብሰብ እንኳን ጊዜ አይሰጧቸውም፡፡ ይህ ወደር የለሽ የጽዮናዊያን ጭካኔ ሴቶችና ህጸናት የተገነዘቡት አሰቃቂ ተሞክሮ ነው፡፡

ሌላው ትዕይንት ደግሞ ሴቶችንና ህጻናትን በመግረፍና በመደብደብ የሚያሰቃዩበት ሁኔታ ነው፡፡እስከዚህ ደረጃ የደረሰው የጭካኔ ተግባር ከማቋረጥ ወይም ከመግታት ይልቅ እንዲቀጥሉበት ምዕራባዊያን ስውር ድጋፋቸውን ይለግሳሉ፡፡ ፍልስጤናዊያን ሴቶችና ህጻናት የሚደርስባቸውን በደል በአደባባይ ለመቃወም ሲወጡ በእስራኤል ወታደሮች ተኩሶ መግደል ለምዕራባዊያን አሸባሪነት አይደለም፡፡ በአንጻሩ ግን ለመብቷ የወጣችውን ሴት አሸባሪ ይሏታል፡፡እስከአፍንጫው የታጠቀ የእስራኤል ወታደር ጠጠር ከሚወረውሩ ለጋ ወጣቶች ጋር በመሯሯጥ ይዞ ሲያሰቃይና ሲገድል በእየ እለቱ በቴሌቭዥን የሚታይ ክስተት ነው፡፡ይህ ትዕይንት ከ 60 ዓመታት በላይ የዘለቀ ሲሆን መጨረሻ ሊበጅለት አልቻለም፡፡ሃያላን ነን ባይ ሀገሮች በየእለቱ የሚፈጸመው አሰቃቂ ትዕይንት ተጠቃሚ ናቸውና፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአስላሙ አለም የተጀመረው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሚያሳየው ነገር ቢኖር የምዕራባዊያንን ሴራ ነው፡፡እነዚህ እስላማዊ ሀገሮች እየደረሰ ያለው የንብረት መውደምና የመዋቅሮች መፈራረስ በአጠቃላይ ኢኮኖሚ ድቀት በየትኛው ዘመን /በምን ያህል ካፒታል ሊተካ እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡

እድገትና ልማት ብሎ ነገር በነዚህ ሀገሮች አይታሰብም፡፡ ፍርስራሽና የቆሻሻ ክምር የሚታይባቸው የጥንት ደማቅ ከተሞች ቁጥራቸው አነስተኛ አይደለም፡፡ ይህ ተጽእኖና ጭቆና የፈጠረው ገጽታ ነው፡፡ የተፈጥሮ አደጋ ከሚያስከትለው ጥፋት የላቀ ነው፡፡በመሆኑም እስላማዊ አለም ሰቆቃውና ብሶቱ ይህነው ተብሎ ሊገለጽ አይችልም፡፡

የተከበራችሁ ምዕራቢያዊያን ወጣቶች በቅርቡ ሆነ አልያም ወደፊት የምዕራባዊያንን የተባላሸ አስተሳሰብ ልትቀይሩ ፣እንደምትቹሉ የተዛባና የተባለሸውን አመለካከት ወደ ጥሩ መንገድ ልታቃኑ እንደምትችሉ አምናለሁ፡፡ የረጅም ጊዜ ግባችሁንና ዓላማችሁን በከፍተኛ ክህሎት

በማጠናከር አስደማሚ ውጤት እንደምታመጡ አምናለሁ፡በተንኮል ጥበብ የተሸፈነውን እርኩስ አላማ ሁለት ገጽታ ያለውን የምዕራባዊያን የማተራመስ አስተሳሰብ የመበጥበጥ ፖሊሲያቸውን ሥርዓት ባለው ሁኔታ ለያይተው መመልከት ካቻሉ ለሰው ልጆች ዋጋ መስጠትን ካልጀመሩ በአገራቸው ውስጥ የብጥብጥና ሽብርን ስር መንቀል ከቶ አይቻላቸውም፡፡

በምዕራባዊያን የፖለቲካ ባህል ሰርጾ የገባ የማተራመስ አባዜ ህዝቦች ሲኮሩበትና ሲመኩበት የኖረውን ባህል አደብዝዞታል፡፡ኢስላማዊ ዓለምም ሳይቀር በዚህ ክልስ ባህል የተበረዘ ነው፡፡ሳይንስና ቴክኖሎጂ ያስገኛቸው ውጤቶች ሰውን በሰውነቱየማክበሩን ዐብይ ነገር አጥፍቶታል፡፡በጎ የሚመስሉ ዲቃላ ባህልን በማወራረስ ራሱን ችሎ የቆየው ባህል ቦታውን እንዲለቅና በብጥብጥና ሽብር እንዲተካ ያለሰለሰ ጥረት አድርገዋል፡፡የህዝቡን መልካም ስነምግባር እርኩስ በሆነ ዓላማ እሴት እንዳይኖረው ሆኗል፡፡

እንደአለመታደል ሆኖከምዕራባዊያን ውጪ ያሉ አገሮችም ስር በሰደደው የጥፋት ተልዕኮ ሰለባ በመሆን የቆየውን መልካም የመተሳሰብና አብሮ በሰላም የመኖር ባህልን አሽቀንጥረው እንዲጥሉት አድርገዋል ፡፡ሳይጎረብጥና ሳይሻክር ሥር የሠደደው የምዕራባዊያን ወረራ ዓለም ለዘመናት የኖረበትን የመከባበር የመተጋገዝና የመተሳሰብ ባህልን ደምስሶታል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢስላማዊ አለም አዲሱን የምዕራባዊያን የባህል ድሪቶ ከመሸከም አልፎ በማባዛት ለብዙ አካባቢዎች ሲያደርሰው ይታያል፡፡የተከበረው የህዝቦች ባህል በምዕራባዊያን ዲቃላ ባህል ተወሮ ለጥላቻና ብጥብጥ ቦታውን ሊለቅ ተገዷል፡፡ተጋፊነትና አይመርጤ የሞራል ክስተት የምዕራባዊያን የባህል መለያ ተምሳሌት እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ይህ የሰው ልጆችን ህልውና አዘቀት ውስጥ የጨመረ አካሄድ የህዝቦችን ባህል ከንቱ ከማድረግ ባሻገር የሐጢያት ማሰብሰቢያ ቋጥ አድርጎታል፡፡ የህዝቡን መልካም የባህል እሴት ከማበልጸግ ይልቅ በአታካራ የተሞላ ቁልቁል የሚጓዝ አደገኛ የምጸት ሃይል ፈጥሯል፡፡

እንደ ዳኤሽ ያሉ ቆሻሻ ቡድኖች ሃይማኖትን በማስታከክ የሚያደርሱት በደል በቀኝ ገዢዎች የተዘራየተንኮል ዘርፍሬ ስለመሆናቸው ጥርጥር የለውም ፡፡በመሰረቱም ያለተጨባጭ ምክንያት የአንድን ሰው ህይወት ማጥፋት መላየሰውን ልጅ እንደመግደል እንደሆነ እየታወቀ ከዚህ የእምነት መሰረት ሀሳብ በመውጣት እየተፈጸመ ያለው ጭካኔ የወለደው ጭፍን ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በምእራባዊያን አገሮች ተወልደው ያደጉና በትምህርታቸው የተካኑ ምሁራን ይህን ዘግናኝ ድርጊት በምን ሁኔታ እያዩትና እየታዘቡት ነው የሚል ጥያቄ አለን፡፡ ወይስ ለድብቅ አጀንዳዎችና ሴራዎች ተባባሪ ናቸው፡፡ ይህን በተመለከተ ከናንተ አሳማኝ ትንተና እንጠብቃለን፡፡ራሳችሁ በፈጠራችሁት ተንኮል በሚፈጠረው አጸፋዊ ምላሽ ያለምንም ጥናትና መረጃ በሀገራችሁ የሚኖሩትን ሙስሊም ዜጎቻችሁን ሰለባ ማድረግ ችግሩን የሚያቃልል ሳይሆን እንዲባባስ ያደርገዋል፡፡እንደኔ መፍትሄው ህዝባችሁ ግልጽ በሆነ ሁኔታ በመቀራረብና በመዋሃድ የግንኙነት ቋጠሮውን ሲያጠብቅ ብቻ ነው፡ የስጋትና የሽብር ሁኔታ የሚስተካከለው ስንጥቁሲሞላና ሲስተካከል እንጂ የበለጠ ሲጎደጉዱና ጥልቀቱ ሲጨምር አይደለም ሰላም የሚገኘው፡፡

በጎ ተጽዕኖዎች ዳብረው የህዝቡን ኑሮ ከማሻሻል ይልቅ ተሽመድምደው በአጭር እንዲቀሩ አድርጔቸዋል፡፡

ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል እንዲሉ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ሰበብ የምትወስዱት እርምጃ ሁሉ ከዳጡ ወደ ማጡ እያመጣችሁ መሆኑን ተረዱት፡፡በመሆኑም አውሮፓና አሜሪካ የሚኖሩ ሙስሊሞች ላይ እየወሰዳችሁት ያለው እርምጃ የሚያዛልቅ አይደለም፡፡ይባሱኑ ወደ ማትወጡበት ችግርውስጥ ትገባለችሁ፡፡

መብትና ክብራቸውን በመጠበቅ ተዋህደውና ተቀላቅለው የሚኖሩበትን ሁኔታ ብታመቻቹ ግን ችግሩ የቀለለ ይሆናል፡፡

ጥናት የጎደለው እርምጃና ውሳኔ ችግሩን ከማባባስ በዘለለ የመራራቁን ክፍተት ያሰፋዋል፡፡ በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች እየተዘጋጁ ያሉ መመሪያዎች ለችግሩ መፍትሄ የሚያመጡ ሳይሆን የሚያባብሱ እንደሚሆኑ አልጠራጠርም ፡፡ሙስሊሙን ዜጋ እንደዜጋ ሳይቆጥሩ ተወላጅ ኑዋሪው በሙስሊሙ ላይ እንዲሰልል እንዲከታተል የሚፈቅደው ኢ- ዲሞክራሳዊ የሆንው መመሪያችሁየሙስሊም ዜጎቻችሁን መብት የሚጋፋ ሽብርን የሚያባብስ አደገኛ አካሄድ እየሄዳችሁ ስለሆነ በተረጋጋ መንፈስ ቆም ብላችሁ ለማስተዋል እንድትሞክሩ ምክሬን እለግሳችዋለሁ፡፡

በመሆኑም እናንተ የምዕራባዊያን ወጣቶች እየታየ ያለውን ያገሮቻችሁን አደገኛ አዝማሚያ ፈጥናችሁ በመረዳት የሙስሊሙ አለም ከእናንተ ጋር መልካም መስተጋብር ፈጥሮ የሚራመድበትን አካሄድ ከጋራ ጥቅምና ሰላም አንጻር የተቃኘ የግንኙነት መሰረት በማጣል የሁለቱም ህዝቦች በልበ ሙሉነትና በመተማመን ላይ በተመሰረተ መርህ እንዲቀናጁ የማድረግ ግዴታ አለባችሁ፡፡ይህ ከሆነ ብቻ ነው ብሩህ የሆነው ተስፋ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ የሚቻለው ዓለም በፍቅር ደምቃ ህዝቦች ፈክተውና በልጽገው መታየት የሚችሉት፡፡

የኢስላማዊ ሩፑብሊክ ኢራን መንፈሳዊ መሪ የሰይይድ አሊ ኻመነይ መልዕክት

በ1394-29 ኖቬምበር, 2015

............................

End/ 101


Post your comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

سخنرانی امام خامنه‌ای به‌مناسبت روز قدس 1399
#AlQudsPathwayofMartyrs
conference-abu-talib